Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የፅህፈት ቤቱ የወጣት ክንፍ የታላቁን ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቦንድ በመግዛት አሻራውን አኑሯል

በሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የወጣት ክንፍ አባላት የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቦንድ በመግዛት አሻራውን አኑሯል።

በብልፅግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የወጣት ክንፍ አባላት የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ግዢ ፈፅመዋል።

የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፉ ሀላፊ ወጣት ሙስጠፋ ኤሊያስ እንደገለፀው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የኢትዮጵያውያን ሁሉ ኩራት የሆነ ግድብ መሆኑን ገልጿል።

ወጣቱ የህዳሴ ግድቡ ከጀመረበት ግዜ አንስቶ ቦንድ በመግዛት አሻራውን ሲያኖር መቆየቱንም አክለዋል።

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያለማንም ድጋፍ ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ ተሰባስበው በአንድነት የገነቡት የአንድነታችን ማሳያ ነው።

ግድቡ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የአገሪቱን ኢኮኖሚ ይበልጥ በማነቃቃት የሀይል አቅርቦት ተደራሽነትን ከማስፋት ባለፈ ለወጣቱ የስራ ዕድል የሚፈጠርበት መሆኑንም ገልጿል።

በመሆኑም ወጣቱ ትውልድ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ እያደረገ የሚገኘውን ድጋፍ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲል መልዕክት አስተላልፏል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እስከሚጀምር ድረስ የወጣት ክንፉ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ወጣት ሙስጠፋ ኤልያስ አረጋግጧል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

hiHarari