የአብሮነት እሴት እንዲጠናከር እና ህዝቡ የልማት ዋና ተዋናይ እንዲሆን በማስቻል ረገድ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራዎችን ማጠናከር ይገባል- አቶ ሔኖክ ሙሉነህ
የክልሉ ህዝብ የአብሮነት እሴት እንዲጠናከር እና ህዝቡ የልማት ዋና ተዋናይ እንዲሆን በማስቻል ረገድ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራዎችን ማጠናከር ይገባል ሲሉ የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ ተናገሩ።
በሀረሪ ክልል ለሚገኙ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያዎች ጋር ውይይት ተካሂዳል።
በውይይቱ ላይ የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ እንደተናገሩት የክልሉ ህዝብ በሰላም፣ በመቻቻልና በአብሮነት የመኖር እሴቶች እንዲጎለብቱ በዲጂታል እና በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ተግባራትን ማጠናከር ያስፈልጋል።
የተጠናከረ የሚዲያ እና የኮሙዩኒኬሽን ስራዎችን በአግባቡ ማከናወን በመረጃ የዳበረ ዜጋ ለመፍጠር እና ህዝቡ በልማትና በዲሞክራሲ ግንባታ ላይ ዋና ተዋናይ እንዲሆን በማስቻል ረገድ የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ሚና የላቀ መሆኑን አንስተዋል።
ህዝቡ በልማትና በዲሞክራሲ ግንባታ ዋና ተዋናይ እንዲሆን በማስቻል ረገድም የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ሚና የላቀ መሆኑን አንስተዋል።
በመሆኑም የሚዲያና ኮሚዩንኬሽን ዘርፉን ሁለንተናዊ አቅም በማጠናከር አሟጥጦ መጠቀም አስፈላጊ መሆኑ ጠቁመው ዘርፉን በሰለጠነ የሰው ኃይል፣ በቁሳቁስና በቴክኖሎጂ በማጠናከር የአስተሳሰብና የተግባር ለውጥ ለማምጣት ቁልፍ መሳሪያ አድርጎ መጠቀም ይገባል ብለዋል።
የኮሙኒኬሽንና ሚድያ ስራዎች በጋራ እሳቤዎች እና ትርክቶች ላይ በመመስረት መስራት እና ሀገርንና ህዝብን ማሻገር የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በማተኮር መስራት እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።
በቀጣይም በክልሉ ዘርፉን በማጠናከር መልካም እሴቶችን እንዲጠናከሩ የሚያስችሉ ስራዎችን በትኩረት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።


0 Comments