የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በሀረሪ ክልል ለ434 ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በሀረሪ ክልል ለ434 የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ናቸው የትምህርት መርጃ ቁሳቁሱን ያበረከቱት።
በሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የተመራው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ልዑክ በሀረር ከተማ የአረንጓዴ አሻራ አኑሯል።
በመርሃግብሩ ላይ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ፣ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሮዛ ኡመርን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።



0 Comments