የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ለከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ተጀመረ
የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ለክልሉ ለከፍተኛ እና ለመካከለኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ተጀመረ
የክልል ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ በወቅታዊ፣ ዓለማቀፋዊ፣ አህጉራዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ዛሬ መስጠት ተጀምሯል፡፡
በመድረኩም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የወረዳ አመራሮች እየተሳተፉበት ይገኛል፡፡
የአቅም ግንባታ ስልጠናው አመራሩ ዓለማቀፋዊ፣ አህጉራዊ፣ ሀገራዊ እና ክልላዊ ወቅታዊ ሁኔታዎችን በአግባቡ ተረድቶ ሀገራዊና ክልላዊ ተልዕኮዎችን በላቀ ሁኔታ ለመፈጸም የሚያስችል አቅም ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡
በተለያዩ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ የሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና ለአራት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይም ተገልጿል፡፡

0 Comments