Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

እውቅናው ለመላው ሰላም ወዳድ ህዝባችን የተሰጠ ነው፦ አቶ ኦርዲን በድሪ

የሀረሪ ክልል የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ያበረከተው እውቅና ለመላው ሰላም ወዳድ ህዝባችን የተሰጠ ነው ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን በድሪ ተናግረዋል።

በሀረር ከተማ በተካሄደው 4ኛው የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሀረሪ ክልል የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እውቅና ማበርከቱ ይታወሳል።

እውቅናውን በሚመለከት ርዕሰ መስተዳድሩ ባስተላለፉት መልዕክት ”የሰላም ጠባቂና ባለቤት ህዝብ ነው” በማለት እውቅናውም ለመላው ሰላም ወዳድ ህዝባችን የተሰጠ ነው ሲሉ የገለፁት።

የተበረከተው እውቅናም ለሰላም፣ ለአብሮነት፣ ለመከባበር፣ ለመተማመን እና ለመቻቻል የበለጠ እንድንተጋ የሚያበረታታን መሆኑን ነው የተናገሩት።

ሀረር በአለም አቀፍ ደረጃ የምትታወቅበትን የሰላም፣ የአብሮነት፣ የመቻቻልና የፍቅር ተምሳሌት ለማድረግ በሰጡት የላቀ አመራር እንዲሁም አራተኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ እንዲሳካ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በሚል ነው የሀረሪ ክልል የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የእውቅና ሽልማት አበርክቷል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

hiHarari