Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-የሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች 

ሐረር፣ግንቦት 12/2017(ሐክመኮ):-ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ገለፁ፡፡ 

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ግዜ አንስቶ ድጋፋቸውን ሲያደርጉ እንደ ነበር የገለፁት ተማሪዎቹ በፕሮጀክቱ ላይ አሻራቸውን በማኖራቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እንደ አይናችን ብሌን የምንጠብቀው በመላው ኢትዮጵያውያን ትብብር በራስ አቅም የተገነባ ፕሮጀክት ነው።

ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ወደ አገልግሎት ሲገባ የኢትዮጵያን የሐይል አቅርቦት ከመሸፈን ባለፈ ገቢ በማመንጨት ለኢኮኖሚው  መነቃቃት ከፍተኛ አበርክቶ ይኖረዋል።

በተለይ የህዳሴ ግድብ ግንባታው ህጻን አዋቂ ሳይለይ ሁሉም የተረባረበበት መሆኑን በመጠቆም በቀጣይም ግንባታው እስኪጠናቀቅ የጀመሩትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

hiHarari