በክልሉ የተመዘገቡ ስኬቶችን በአዲሱ የ 2018 በጀት ዓመት በማስፋት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማስፋት ይሰራል-አቶ ጌቱ ወዬሳ
በሀረሪ ክልል በሁሉም ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን በአዲሱ የ 2018 በጀት ዓመት በማስፋት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማስፋት እንደሚሰራ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለፁ።
በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት በክልሉ የተመዘገቡ ስኬቶችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።
ሀላፊው በሰጡት መግለጫ የተጠናቀቀው የ 2017 በጀት ዓመት ሰውን ማዕከል ያደረጉ የልማት ስራዎችን በማከናወን አበረታች ውጤት የተመዘገበበት የስኬት ዓመት አንደነበር ገልፀዋል።
በክልሉ የተመዘገቡ ለውጦች ብልጽግና ፓርቲ ለህዝቡ የገባውን ቃል በተግባር እየተረጎመ ለመሆኑ ማሳያ ተደርገው ሊወሰዱ የሚችሉ መሆናቸውንም ገልፀዋል።
በተለይ ኮሪደር ልማት፣በኢኮኖሚ፤ በሰላም እሴት ግንባታ፤ በቱሪዝምና አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ ተጨባጭ ለውጦች የተመዘገቡበት እንደነበር አስታውሰዋል።
የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት መቻሉንም ጠቁመዋል።
በተለይ ምቹ የስራ አካባቢን ለመፍጠር ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ በተከናወኑ ተግባራት በክልሉ ዘጠኙም ወረዳዎች የፓርቲ ፅ/ቤት በመገንባት አበረታች ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን ገልፀዋል።
ፓርቲው በዕውቀትና ስነ ምግባር የታነፀ አገልጋይ አመራርና አባላትን ለመፍጠር ተከታታይ ስልጠናዎችን ከመስጠት ጀምሮ ውይይቶች ሲደረጉ መቆየቱን ገልፀዋል።
ይህም በመደበኛ ተግባራት ብሎም በፓርቲ ስራዎች ላይ አመርቂ ውጤቶች እንዲመዘገቡ ማስቻሉን በመጠቆም ውጤቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ለማድረግ በትኩረት ይሰራል።
በተለይ በክረምት የበጎ ፈቃድ ተግባራት ማህበረሱብን ተጠቃሚ ያደረጉ ሰው ተኮር የልማት ስራዎችን በመተግበር ውጤት ማስመዝገቡን ገልፀዋል።
በቀጣዩ የ 2018 በጀት ዓመትም ባለፉት ዓመታት በዕቅድ ተይዘው ያልተከናወኑ ተግባራትን ለማካካስ በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል።
እየጨመረ ለመጣው የማህበረሰብ የልማት ጥያቄ ምላሽ መስጠት እንዲቻል የገቢ ምንጮችን አሟጦ ተጠቅሞ የመንግስት ገቢን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ገልፀዋል።
0 Comments