Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ የመረጃ ተደራሽነትን በማጎልበት ረገድ አበረታች ተግባራት ተከናውነዋል-አቶ ሔኖክ ሙሉነህ

ሐረር፤የካቲት 5/2017(ሀክመኮ):-በሀረሪ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት የመረጃ ተደራሽነትን በማጎልበት ረገድ አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ ገለፁ። 

የሀረሪ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት የተቋሙን የመረጃ ተደራሽነት በማጎልበት በህዝብና መንግስት መካከል ሁነኛ የመረጃ ድልድይ ሆኖ ተግባቦትን የመፍጠር ስራዎችን ማከናወን መቻሉን የ ፅ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ አስታውቀዋል።

ወቅታዊ እና አገራዊ መረጃዎችን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ከማድረግ ባለፈ የአፍራሽ ሀይሉን አጀንዳ በማምከን ረገድ አበረታች ስራዎች መከናወናቸውንም ተናግረዋል። 

የሚዲያ ሞኒተሪንግ፣ የህዝብ አስተያየት ጥናት እና የህትመት ዝግጅትና ስርጭት ስራዎች ላይም በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል። 

በተለይ በክልላዊና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ከመፍጠር አንጻር የኮሙዩኒኬሽን ዘርፉ የድርሻውን እንዲወጣ ለማስቻል ጥረት መደረጉን አስረድተዋል። 

በክልሉ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦች እንዲተዋወቁ እንዲሁም የክልሉ ህዝብ በሰላም፣ በመቻቻልና በአብሮነት የመኖር እሴቶች ይበልጥ እንዲጎለብቱ ለማስቻል በተለያዩ የሚዲያ አመራጮች የተግባቦት ስራ ሲሰራ መቆየቱንም ጠቁመዋል።

በክልሉ የሚከናወኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎችን በተመለከተም የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ግንዛቤ በመፍጠር ማህበረሰቡ በልማት ስራው ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ማስቻሉን አስገንዝበዋል።

በተቋማትና ወረዳዎች በኮሙዩኒኬሽን ዘርፉ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመቅረፍና መልካም አፈጻጸሞችን ለማጎልበት በተከናወኑ ተግባራት መነቃቃቶች መፈጠራቸውንም ገልፀዋል።

በቀጣይም ተቋሙ የተቋቋመለትን ዓላማ በብቃት ለመወጣትና የመረጃ ተደራሽነቱን ይበልጥ በማጎልበት የጀመራቸውን አበረታች ተግባራት አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል አቶ ሔኖክ ሙሉነህ ገልፀዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

hiHarari