በሀረር ከተማ የተከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች ስላም ካለ አገርን ተባብሮ ማሳደግ እንደሚቻል ያሳየ ነው-የሀይማኖት አባቶች
በሀረር ከተማ የተከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች ስላም ካለ አገርን ተባብሮ ማሳደግ እንደሚቻል በተግባር ያሳየ መሆኑን የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ።
በ4ተኛው አገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ ተሳታፊ የሀይማኖት አባቶች በሀረር ከተማ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ተመልክተዋል።
የሀይማት አባቶቹ በጁገል አለም አቅፍ ቅርስ ውስጥና ዙሪያ እና በከተማ በተለያዩ አካባቢዎች የተከናወኑና እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ተዘዋውረው ተመልክተዋል
በመስክ ምልክታው ላይም በተለይም በአለም አቀፉ የጁገል ቅርስ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች ቅርሱን ከአደጋ ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ የሚያስችል የሚደነቅ ስራ መከናወኑ መመልከታቸውን ገልፀዋል።
በተለይ ቅርሱን ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ ለኑሮ ብሎም ጎብኚዎች በሚመችና ባማረ መልኩ መከናወኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል።
ይህም ትውልዱ ከአባቶቹ የተረከበውን ታሪክ ጠብቆ በማቆየት ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ዕድል የፈጠረ ነው ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች እውን የተደረጉና በመገንባት ላይ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች ከተማው በአስደናቂ የልማት ጉዞ ላይ መሆኗን የሚያረጋግጡ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።
በከተማው ጥንታዊውን ከዘመናዊው ጋር ባዋሃደ መልኩ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ለሌሎችም ጥንታዊና የቅርስ ከተሞች በተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑ አንስተዋል
በክልሉ የሰፈነው ሰላም ለልማት ስራዎች ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል ያሉት የእምነት አባቶቹ በከተማው የተከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች ሰላም ካለ አገርን ተባብሮ ማሳደግ እንደሚቻል በተግባር ያሳዩ ናቸው ብለዋል።
በመስክ ምልከታቸው ሀረር የፍቅር፣ አብሮነትና የሰላም ከተማ መሆኗን በተግባር ማረጋገጥ መቻላቸውን ነው የጠቆሙት።
የሀይማኖት አባቶቹ ሀረር ኢኮ ፓርክ በመጎብኘትም የችግኝ ተከላ ያከናወኑ ሲሆን በጉብኝት በመርሃግብሩ ላይም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ለአገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ ተሳታፊ የሀይማኖት አባቶች በሀረር ኢኮ ፓርክ የእራት ግብዣ መርሃግብርም ተደርጎላቸዋል።
በሀረር ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው 4ተኛው አገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ በነገው እለትም እንደሚቀጥል ተገልጿል።
0 Comments