Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሀረሪ ክልል የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ – ኮሚሽነር አህመድ አብዲ

በሀረሪ ክልል ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ ማህበረሰቡን ያሳተፈ የወንጀል መከላከል ስራ በማጠናከር በክልሉ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ኮሚሽነሩ በቀጣዩ 2018 በጀት አመት በሚከናወኑ አበይት ክንውኖች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በሰጡት መግለጫ እንዳመላከቱት በ2017 በተከናወኑ በተለያዩ ስራዎች የክልሉን አንፃራዊ ሰላም ማስቀጠል ተችሏል።

በ2018 የበጀት አመት በክልሉ የሰፈነውን አንፃራዊ ሰላም ወደ ዘላቂ ሰላም ለማሳደግ እና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎች በትኩረት እንደሚሰራገልፀዋል።

የተቋሙ የወንጀል መከላከል አቅምን በቴክኖሎጂ የመደገፍ እንዲሁም የፖሊስ የወንጀል መከላከል ተግባርን በተለያየ የስራ ዘርፎች የማዋቀር እንዲሁም ድንገታዊ የወንጀል ክስተቶች ሲያጋጥሙም ውጤታማ የምርመራ ሂደቱን ለማካሄድ የሚያስችሉ ስራዎች ለማከናወን ትኩረት ተሰጥቷል እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ከዚህ ባሻገርም የማህበረሰቡን የወንጀል መከላከል ግንዛቤን ለማሳደግ የተለያዩ ስልጠናዎችን ለመስጠት መታቀዱን ጠቁመዋል።

በዚህም በክልሉ በሚገኙ በሁሉም ቀበሌዎች የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎትን ለማሳደግ ሚናው የላቀ ስለመሆኑ አንስተዋል።

ተቋሙ በክልሉ በትራፊክ አደጋ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመቀነስ እየተሰራ ስለመሆኑ የጠቆሙ ሲሆን ለዘህም

የትራፊክ ቁጥጥር አቅምን በማሳደግ በትራፊክ የሚጣሱ ደንቦችን እንዲቀንሱ እና ህግ የማስከበር የማስከበር ስራዎች በትኩረት ይከናወናሉ ብለዋል።

ኮሚሽኑ በስነምግባር የታነፀ እንዲሁም በእውቀት የበለፀገ የፖሊስ አባላት እንዲኖሩ ለማስቻል እየተደረጉ የሚገኙ የክትትልና የቁጥጥር ተግባራት እንደሚጠናከሩ ነው የተናገሩት።

ህብረተሰቡም በክልሉ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥና ቀጣይነት ያለው ሰላም ለማስፈን በሚከናወኑ ተግባራት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

hiHarari