Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሀረሪ ክልል ሕብረተሰቡን ያሳተፈ የ”ትምህርት ለትውልድ” መርሃግብር ስራዎች እየተከናወኑ ነው- የክልሉ ትምህርት ቢሮ

በሀረሪ ክልል ሕብረተሰቡን ያሳተፈ የ”ትምህርት ለትውልድ” መርሃ ግብር ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ እንደገለጹት፥ በክልሉ “በትምህርት ለትውልድ” መርሃ ግብር የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ባለድርሻ አካላትንና ህብረተሰቡን በማስተባበር እየተሰራ ነው።

በዚህም የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶችን በማደስ ጽዱና ለመማር መስተማር ስራው ምቹ የማድረግና የመምህራን መኖሪያ ቤት ግንባታ፣ የጉድጓድ ውሃ ቁፋሮ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።

እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው አነስተኛ ለሆኑ ህጻናት የትምህርት ቁሳቁስ ማሰባሰብ፣ የትምህርት ማጣቀሻ መጻህፍትን፣ የግብዓት ችግርን መፍታት፣ ለተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አመልክተዋል።

“በትምህርት ለትውልድ መርሃ ግብር የሚከናወኑ ስራዎች የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሻሻል ባለፈ ተማሪዎች በአግባቡ ትምህርታቸውን ለመከታተል በማስቻሉ የትምህርት ጥራቱ እንዲረጋገጥ የራሱን አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በክልሉ የ2018 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ በሁሉም የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ መጀመሩን የተናገሩት አቶ ጌቱ፤ በክልሉ መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ትምህርት እንደሚጀመርም ገልጸዋል።

በሀረሪ ክልል በ2018 የትምህርት ዘመን ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ 92ሺህ ተማሪዎች ተመዝግበው ትምህርታቸውን ይከታተላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Harari #Education #News #ዜና

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

hiHarari