ለትምህርት የደረሱ ህፃናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ ሁሉም ሀላፊነቱን በመወጣት ሊረባረብ ይገባል-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ
ለትምህርት የደረሱ ህፃናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ ሁሉም ሀላፊነቱን በመወጣት ሊረባረብ ይገባል እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የ 2018 መደበኛ ትምህርት በክልሉ ሁሉም ትምትርት ቤቶች ከመስከረም 5 ጀምሮ መሰጠት አንደሚጀመር ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ወደላቀ ከፍታ በማድረስ ማህበራዊ ብልፅግናን በማረጋገጥ የጀመርነውን ጉዞ እውን ለማድረግ ትውልዱን በዕውቀት መገንባትና ማነፅ ያስፈልጋል።
ለዚህም የክልሉ መንግስት የትምህርት ጥራትን በማሻሻል ብቁና አምራች ዜጋ ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።
የጀመርነውን አገራዊ ሪፎርም በማጠናከር የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማስፋት ለትምህርት የደረሱ ልጆች ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ ከምንግዜውም በላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።
ለትምህርት የደረሱ ህፃናት ወደ ትምህርት ቤት መግባት መብታቸው ሲሆን ወላጆች ልጆቻቸውን የማስተማር ግዴታ ያለባቸው በመሆኑ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት ሊልኩ ይገባል።
በተለይ በ 2017 የትምህርት ዘመን ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎችን ጨምሮ ሁሉም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ወላጆች፣መምህራንና ባለድርሻ አካላት የጀመሩትን ንቅናቄ አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በተያዘው የ2018 የትምህርት ዘመን በክልሉ ከ 92 ሺ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅት ተደርጓል።
በመሆኑም ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆች ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ በማድረግ ሁሉም የበኩሉን ሀላፊነት እንዲወጡ ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።
0 Comments