Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ በሐረር ከተማ ይካሄዳል

አራተኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ ሐምሌ 28 እና 29 ቀን 2017 ዓ.ም በሐረር ከተማ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የሰላም ጉባኤውን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ ጉባኤው በሃይማኖት ተቋማት መካከል ያለውን ትስስር ያጠናክራል ብለዋል።

በመድረኩ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች እንደሚገኙ ገልጸዋል።

የሰላም ጉባኤው በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት አስተዋጽኦ ይኖረዋል ነው ያሉት።

በተጨማሪም ችግሮችን በውይይት የመፍታት ልምዶችን ለማዳበር ወሳኝ መሆኑን አመልክተው፤ በጉባኤው የፓናል ውይይቶችና ህዝባዊ ኮንፈረንስ እንደሚኖር ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም በድሬድዋ፣ በጅማ፣ በባህርዳር በተካሄዱ የሰላም ጉባኤዎች ህብረተሰቡ የሰላም ባለቤት እንዲሆን የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውን አስታውሰዋል።

በተለይም የሃይማኖት ተቋማት እርስ በርስ በመቀራረብ የመደጋገፍ ባህል አዳብረዋል ብለዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

hiHarari