ለ26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን እንግዶች ወደ ሀገር ቤት እየገቡ ነው
በተለያዩ አለማት የሚገኙ ሀረሪዎችና የሀረር ተወላጆች ለ26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን ለመሳተፍ ወደ ሀገር ቤት እየገቡ ይገኛሉ።
እንግዶች ወደ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱም በሀረሪ ክልል አመራሮች አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።
በሀረር ከተማ የሚከበረው የዘንድሮው 26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን 15 ቀናት ይቀሩታል።