በክልሉ በኢኮኖሚ ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶች የሀረርን የማንሰራራት ጅማሮ የሚያሰፉ ናቸው-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ
ሀረር፣ጥቅምት 11/2018(ሀክመኮ):-በሀረሪ ክልል በኢኮኖሚ ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶች የሀረርን የማንሰራራት ጅማሮ የሚያሰፉ መሆናቸውን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።
በሀረሪ ክልል የሚገኙ የኢኮኖሚ ዘርፍ ተቋማት የ2018 1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ተገምግሟል።
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በግምገማው ላይ እንደገለፁት በአንደኛው ሩብ ዓመት በኢኮኖሚ ዘርፍ በተከናወኑ ተግባራት ተስፋ ሰጪ ስኬቶች ተመዝግበዋል።
በተለይ በዘርፍ የተጀመሩ ስራዎች እና የተመዘገቡ ውጤቶች ለሀረር የማንሰራራት ጉዞ መነሻ የሚሆኑ ናቸው ብለዋል።
2017 በክልሉ በልዩ ሁኔታ ስኬት የተመዘገበበት ነበር ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የ2018 በጀት ዓመት የተጀመረውን የማንሰራራት ጅማሮ የምናሰፋበት ነው ሲሉ ገልፀዋል።
በተለይ ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን በመጠቆም ለአርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ድጋፍ በማድረግና በማገዝ የግብርናና የሌማት ትሩፋት ምርታማነትን ይበልጥ ለማስፋት ይሰራል።
የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍም ለስራ ዕድል ፈጠራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በልላ በኩል በክልሉ ኢንቨስትመንት ዘርፍ መነቃቃትና መሻሻሎች መኖራቸውን በመጠቆም አሁንም የድጋፍና ክትትል ስራውን ማጠናከር ያስፈልጋል።
በተለይ በክልሉ የሚገኙ ኢንቨስትመንቶችን ለክልሉና ማህበረሰቡ እያበረከቱት ካለው አስተዎፆ አንፃር መምራትና ማስተዳደር ይገባል ብለዋል።
በክልሉ አቅርቦትን በማሰደግ የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነትን በአግባቡ ማስተዳደርና መምርት በተለይ ምርት በሚያሸሹና አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በተጠናቀቀው የ2018 1ኛ ሩብ ዓመት ተንጠባጠበው የቀሩ አንዳንድ ቀሪ ስራዎችን በዕቅድ በመያዝ በማካካስ እንዲሰራም አሳስበዋል።
0 Comments