Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

3ተኛው ዙር የጁገል ኮሪደር መልሶ ልማት ስራ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ደርሷል-ኢንጅነር አሚር ረመዳን

ሐረር፣ግንቦት 27/2017(ሐክመኮ):-3ተኛው ዙር የአለም አቀፉ የጁገል ኮሪደር መልሶ ልማት ስራ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን በሐረሪ ክልል ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ የቅርስ ዳይሬክተር ኢንጅነር አሚር ረመዳን አስታወቁ።

አለም አቀፉ የጁገል ኮሪደር የመልሶ ልማት ስራ በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የሐረሪ ክልል ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ የቅርስ ዳይሬክተር ኢንጅነር አሚር ረመዳን ገለፁ።

በ 3ተኛው ዙር አለም አቀፉ የጁገል ኮሪደር መልሶ ልማት ስራ ከ 5 ኪሎ ሜትር በላይ መንገዶችን መልሶ ለማልማት ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን የገለፁት ዳይሬክተሩ የመልሶ ልማት ስራው በቅርቡ ተጠናቆ ክፍት እንደሚሆን አስታውቀዋል።

የመልሶ ልማት ስራውን በ 3 ወራት ግዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዞ ወደ ስራ መገባቱን በማስታወስ ጥራትና ፍጥነትን መሰረት ባደረገ መልኩ የመልሶ ልማት ስራው መከናወኑን ገልፀዋል።

የመልሶ ልማት ስራው ቅርሱ ታሪካዊ ይዘቱን ሳይለቅ በአካባቢው የሚገኙ ፀጋዎችና እውቀትን በመጠቀም የተከናወነ መሆኑንም አክለዋል።

የጁገል ኮሪደር መልሶ ልማት ስራ በአንደኛና ሁለተኛ ዙር ተግባራዊ ከተደረጉ የኮሪደር ልማት ስራዎች የተገኙ ልምዶችን በመቀመር የተከናወነና ስራዎችን በምሽት ጭምር በማከናወን የስራ ባህልን የቀየረ መሆኑንም አክለዋል።

በቅርቡ የመልሶ ልማት ስራውን ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ተመርቆ ክፍት እንደሚደረግም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

3ተኛው ዙር የጁገል ኮሪደር መልሶ ልማት ከ 5 ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ ለማልማት መጋቢት 19 ዕጣ በማውጣት ወደ ስራ መገባቱ ይታወሳል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish