Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን አብሮነት እና አንድነትን በሚያጎለብት መልኩ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው- ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

ሀረር ሰኔ 6/2016(ሀክመኮ) :- 26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን አብሮነት እና አንድነትን በሚያጎለብት መልኩ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ስፖርትና ፌስቲቫል ለማክበር የተቋቋመው ኮሚቴ ለበዓሉ እየተደረጉ የሚገኙ ዝግጅቶችን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በተገኙበት ገምግሟል።

በዓሉ የተሳካ እንዲሆን ለማስቻል የተለያዩ ኮሚቴዎች ተቋቁመው ወደ ስራ የገቡ ሲሆን ከቦታ ልየታ ጀምሮ ለበአሉ አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

በዓሉ በሲምፖዚየም፣ የንግድ ትርዒት እና ባዛር፣ ታሪካዊ እና ባህላዊ ስፍራዎች ጉብኝት፣ በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር፣ የልማት ፕሮጀክቶች ምረቃ እና ሌሎች መርሀ ግብሮች እንደሚከበርም ተገልጿል።

በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ለማስቻልም ከፌዴራል እና አጎራባች ክልል የፀጥታ ተቋማት ጋር እየተሰራ መሆኑን ኮሚቴው አስታውቋል።

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንዳሉት በዓሉ አንድነት እና አብሮነትን በሚጠናከር ብሎም ዘላቂ ሰላም እና ልማትን በሚያረጋግጥ መልኩ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

በተለይ በዓሉ በክልሉ መከበሩ ዲያስፖራው ማህበረሰብ በአገሩ ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በተግባር እንዲገነዘብ ከማድረግ አንፃር ትልቅ አበርክቶ እንደሚኖረው ጠቁመዋል።

በበዓሉ ወቅት የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ለማስመረቅ እየተሰራ እንደሚገኝ የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ በሂደት ላይ የሚገኙ የልማት ስራዎችን በተያዘላቸው ግዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ ሊደረግ ይገባል ብለዋል።

በተለይ አሁን ላይ ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ የከተማ ፅዳት ውበት እና አረንጓዴ ልማት ስራዎች ግለታቸውን ጠብቀው እንዲቀጥሉ ርዕሰ መስተዳድሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish