20ኛውን የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የክልሉን ልማትና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በሚያጎለብቱ መር-ግብሮች ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው-ምክትል አፈ-ጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድ
ሀረር፣ጥቅምት 24/2018(ሀክመኮ):-20ኛውን የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የክልሉን ልማትና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በሚያጎለብቱ መርሀ-ግብሮች ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድ ገለፁ።
የብሄር ብሄረሰቦች ቀን መከበሩ እንደ ሀገር አንድነትን በማጎልበት የጋራ ትርክትን በመገንባት የወንድማማችነት እሴት እንዲጎለብት በማድረግ ከፍተኛ ሚና ማበርከቱን ገልፀዋል።
ዘንድሮ ለ 20ኛ ግዜ የሚከበረውን በዓሉንም አብሮነትና ወንድማማችነትን ይበልጥ አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
በተለይ በዓሉን የክልሉን ልማትና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በሚያጎለብቱ መርሀ-ግብሮች ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ነው ምክትል አፈ ጉባኤው የገለፁት።
በዓሉ በፌዴራሊዝምና ህገ መንግስት አስተምህሮት የፓናል ውይይቶች፣በስፖርታዊ ውይይቶች፣በፅዳት ዘመቻ፣በደም ልገሳ፣በጥያቄና መልስ ውድድሮች፣በሙዚየም ጉብኝት፣የገጠር ኮሪደር ልማቶችን በጉልበት በማገዝ፣በተቋማትና ትምህርት ቤቶች በባሀላዊ ምግቦችና ውዝዋዜዎች ይከበራል ብለዋል።
መሰል መርሀ-ግብሮች ማህበበረሰቡን ይበልጥ እንዲቀራረብ በማድረግ እርስ በዕርስ የመደጋገፍ እና የመረዳዳት ባህሎች ይበልጥ እንዲጎለብቱ የሚያስችል መሆኑንም ገልፀዋል።
20 ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በሆሳህና ከተማ”ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ይከበራል።
0 Comments