Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የፀጥታ ተቋማት ነፃና ገለልተኛ በመሆን ሁሉንም በእኩልነት ሊያገለግሉ ይገባል -ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ 

ሐረር፣ግንቦት 27/2017(ሐክመኮ):-የፀጥታ ተቋማት ነፃና ገለልተኛ በመሆን ሁሉንም በአንድ አይን አይተው በእኩልነት ሊያገለግሉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

በሐረሪ ክልል “የፀጥታ ዘርፍ ሚና ለዘላቂ ሰላም”በሚል መሪ ቃል ከፅጥታ ተቋማት ጋር ውይይት ተካሂዷል።

በውይይት መድረኩ ላይ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የፀጥታ ተቋማት ወቅቱን የዋጁ ሆነው ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲትጡ ለማስቻል የተከናወኑ ተግባራት ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በውይይት መድረኩ ላይ እንደገለፁት የክልሉ መንግስት የፀጥታ ተቋማትን ስራ ለመደገፍ  ሪፎርም ከማድረግ ጀምሮ አበረታች ተግባራት ተከናውነዋል።

በተለይ ከለውጡ ወዲህ የክልሉ መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት ከተሽከርካሪ ጀምሮ ዘርፉን በአስፈላጊ ግብዓቶች የማደራጀት ስራ ማከናወኑን ገልፀዋል።

በተለይ የፖሊስ አሰራርን ለማዘመን ከ 1 መቶ ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የደህንነት ካሜራዎችን በመትከል የፖሊስ ስራን ከፍ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።

በቀጣይም ለፖሊስ ሰራዊቱ ምቹ የስራ ቦታ ለመፍጠር ይሰራል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይ በኤረር እና አሚር ኑር ወረዳዎች ያለውን የጣቢያ ችግር ለመቅረፍ አዲስ ጣቢያዎች እንደሚገነቡ ጠቁመዋል።

በመሆኑም ከፖሊስ ነፃና ገለልተኛ በመሆን ሁሉንም በአንድ አይን አይቶ በእኩልነት ማገልገል እንደሚጠበቅ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሁሉም ዜጋ ለህግ መገዛት አለበት፣ከፀጥታ ተቋማትም ለህግ ተገዢ በመሆን ህግን ማስከበር እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።

የክልሉ መንግስት የፀጥታ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ለማዘመን በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት እንደሚሰራም ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish