Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ ክብርና ተገቢውን ከፍታ አስጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የአሁኑ ትውልድ ኃላፊነት ነው – አፈ ጉባኤ ሱልጣን አብዱሰላም

በሀረሪ ክልል “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮያ ሕዳሴ!” በሚል መሪ ቃል 18ኛው የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በነገው እለት ይከበራል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም በሰጡት መግለጫ የብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በሠንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 863/2006 (በተሻሻለው) አንቀጽ 2 መሰረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ መጀመሪያ ሳምንት ሰኞ እንደሚከበር መደንገጉን ገልጸዋል።

ትውልዱ የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ ክብርና ተገቢውን ከፍታ አስጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ገልጸዋል።

ሠንደቅ ዓላማ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ የታተመ የሀገራዊ አንድነትና ነፃነት መገለጫ ታላቅ የብሔራዊ ኩራት አርማ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ሠንደቅ ዓላማ በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ቦታ ተሰጥቶት የሚከበር ታላቅ ሀገራዊ በዓል መሆኑን አፈ ጉባኤው ገልጸዋል።

በመሆኑም የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ ክብርና ተገቢውን ከፍታ አስጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ሀገራዊ ሉዓላዊነትንና የግዛት አንድነትን ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።

እንደ አፈ ጉባኤው ገለጻ ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት በማጽናት የሀገሪቷን የዕድገት ከፍታ ማረጋገጥ ከአሁኑ ትውልድ የሚጠበቅ ታላቅ ሀገራዊ ኃላፊነት ነው።

የሠንደቅ ዓላማ ቀን መከበሩ ሕብረ ብሔራዊ አንድነታችንና ሉዓላዊነታችን በማስጠበቅ የኢትዮጵያን የከፍታ ብሥራትና ሕዳሴ ለማረጋገጥ ለሀገር ክብርና ጥቅም ሁሉም ዜጋ የሚጠበቅበትን ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት በሠንደቅ ዓላማ ፊት ዳግም ቃሉን የሚያድስበት ዕለት መሆኑን ገልጸዋል።

ነገ ጥዋት ከረፋዱ 4:30 ሠዓት ላይ በሀረሪ ክልል በሚገኙ ሁሉም መንግስታዊና መንግታዊ ያልሆኑ ተቋማት ፣ በትምህርት ቤቶች እና በሌሎች ተቋማት ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል እና በሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ መሐላ በመፈፀም ተከብሮ እንደሚውል ገልጸዋል።

የዘንድሮው ብሄራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሚከበርበት ወቅት ለሰንደቅ ዓለማ ክብር፣ ለሀገር አንድነት፣ ሉዓላዊነት ፣ ክብርና ጥቅም የተከፈለዉን መሥዋዕትነትን ዜጎች እንዲረዱ በማድረግ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish