Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ከፍተኛ መሻሻል ተመዝግቧል-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

ሀረር፣ጥቅምት 10/2018(ሀክመኮ):-በሀረሪ ክልል የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ከፍተኛ መሻሻል መመዝገቡን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ከካቢኔያቸው ጋር በክልሉ በግንባታ ላይ የሚገኙ፣የተጠናቀቁና አዳዲስ ካፒታል ፕሮጀክቶች ላይ የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

በመስክ ምልከታው ማጠቃለያ ላይ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለፁት በተያዘው የ2018 በጀት ዓመት የህዝብን ተጠቃሚነት ይበልጥ የሚያረጋገጡ የልማት ስራዎች በዕቅድ ተይዘው እየተሰሩ ነው።

በክልሉ ከ2018 በጀት 53 በመቶውን ለኢኮኖሚ ዘርፍ በመመደብ ወደ ስራ ተገብቷል።

በክልሉ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የሚታዩ ስራዎችን አጠናክሮ ኢኮኖሚውን ይበልጥ በማነቃቃት የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል።

በክልሉ በካፒቲል ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ከፍተኛ መሻሻል መኖሩን መገምገሙን በመጠቆም ፕሮጀክቶቹ በህዝቡ ህይወት ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ እና የሀረርን የማንሰራራት ጅማሮ የሚያመላክቱ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በክልሉ ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን ወደ ስራ ያልገቡና ያልተጠናቀቁ ካፒታል ፕሮጀክቶች በአጭር ግዜ ተጠናቀው ወደ ስራ እንዲገቡ አቅጣጨ መቀመጡን ገልፀዋል።

በክልሉ የተፈጠረውን አስቻይ ሁኔታ በመጠቀም በ2018 በጀት ዓመትም የክልሉን ገፅታ በመሰረታዊ መልኩ የሚቀይሩ ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል።

በ2018 በጀት ዓመት ለማከናወን በዕቅድ የተያዙ ፕሮጀክቶች የዝግጅት ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን በመጠቆም በቀጣይ በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቁመዋል።

በክልሉ የካፒታል ፕሮጀክቶች መሻሻሎች ቢኖሩም ብዙ ያልሰራናቸው ውዝፍ ስራዎች አሉ ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይ ያልተሰሩ ስራዎችን በማካካስ ለትውልድ ምንዳን ለማውረስ በቁጭት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish