Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ የሚያስችሉ ስራዎች ተከናውነዋል- የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

በሀረሪ ክልል በተጠናቀቀው የበጀት አመት የህዝቡን የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተናግረዋል።

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 8ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ይገኛል።

በጉባኤው ላይ የክልሉ መንግስት በ2017 የበጀት አመት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ስራዎች በሚመለከት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ለምክር ቤቱ ሪፖርት አቅርበዋል።

ባቀረቡት ሪፖርትም በተጠናቀቀው የበጀት አመት በክልሉ የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል።

አምራቹና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት በተለይም በቅዳሜና እሁድ ገበያ ህብረተሰቡ የግብርና ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ የማድረግ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።

ከመሰረታዊ ሸቀጦች አቅርቦትና ስርጭት ጋር ተያይዞም 161,128 ሊትር ዘይትና 920 ኩንታል ስኳር በህብረት ስራ ማህበራትና በዩኒየኖች አማካኝነት ለህብረተሰቡ ተደራሽ መደረጉን ነው ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው የገለፁት።

ከዚህ ባሻገርም ያልተገባና ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 321 የንግድ ድርጅቶች እንዲታሸጉ ከመደረጉም በተጨማሪ የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ተላልፈው  የተገኙ 11 የንግድ ድርጅት ባለቤቶች በህግ እንዲጠየቁ ተደርጋል።

2590 የንግድ ድርጅቶች ደግሞ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ጠቁመው በህገወጥ የነዳጅ ሽያጭ ላይ የተሰማሩ 2 የነዳጅ ማደያዎች ለ3 ወር እንዲታገዱ ተደርጓል ብለዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish