Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መሰጠት ጀመረ

ሐረር፣ሰኔ 3/2017(ሐክመኮ):-በሐረሪ ክልል የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መሰጠት ጀመረ።

ፈተናውን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በቤተልሔም ትምህርት ቤት በመገኘት አስጀምረዋል።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፈተናውን ባስጀመሩበት ወቅት እንደጉፁት በክልሉ የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል።

በተለይ የተማሪዎችን የማለፍ ምጣኔ ለማሳደግ ተማሪዎችን ለፈተና ለማብቃት ትኩረት በመስጠት ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመዋል።

ተማሪዎች ፈተናውን ሳይረበሹ በተረጋጋ መንፈስ እንዲወስዱም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ በበኩላቸው በዘንድሮው የስምንተኛ ክፍል ፈተና ከ 5 ሺ 250 በላይ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም 221 የማታ ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።

በዘንድሮው የ8ተኛ ክፍል ፈተና ከአምናው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል።

ለዚህም ተማሪዎች የተለያዩ የማጠና ከሪያ ትምህርቶችን ብሎም የሙከራ ፈተናዎችን እንዲወስዱ በማድረግ ለፈተና የማዘጋጀት ስራ ሲሰራ መቆየቱን አክለዋል።

ተማሪዎች በፈተና ወቅት ሳይረበሹ ለፈተና እንዲቀመጡ ለማስቻል የማይንድ ሴት ስልጠና መሰጡትንም ተናግረዋል።

ፈተናው በክልሉ በ19 የፈተና ጣቢያዎቸ እየተሰጠ እንደሚገኝና ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish