Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ ከ9 ሺ በላይ ወጣቶች ኮደርስ ስልጠና ወስደዋል -የሀረሪ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ 

ሀረር ግንቦት 26 /2017(ሀክመኮ):- በሐረሪ ክልል ከ9 ሺ በላይ የሚሆኑ  ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መውሰዳቸውን የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ገለፀ 

የኤጀንሲው ሀላፊ አቶ ጀማል ኢብራሂም የኮደርስ ስልጠናው የዜጎችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት በማዳበር እንደ ሀገር ለተጀመረው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ፋይዳው የላቀ ነው።

በተያዘው የ2017 የበጀት ዓመት ለ6755 ወጣቶች ስልጠናውን ለመስጠት ታቅዶ እስካሁን ከ9 ሺ በላይ ወጣቶች ስልጠናውን መውሰዳቸውን ጠቁመዋል። 

እስካሁን በኢኒሼቲቩ በተሰራው ስራ በክልል ደረጃ ስልጠናውን ካጠናቀቁ ወጣቶች መካከል ከ5 ሺህ የሚሆኑት የምስክር ወረቀት መውሰዳቸውን ጠቅሰዋል።

በመርሀ ግብሩም ፕሮግራሚንግ፣ ዳታ ሳይንስ፣ አንድሮይድና ተያያዥነት ያላቸው ስልጠናዎች እየተሰጠ መሆኑንም ገልጸዋል። 

ሥልጠናው ወጣቶችን የክህሎት ባለቤት ከማድረግ ባለፈ ብቁ፣ ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል። 

ስልጠናው ወጣቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችል በሆኑ ስልጠናውን ያልወሰዱ በቀጣይ ግዜያት ተመዝግበው እንዲሰለጥኑ ሀላፊው ጥሪ አስተላልፈዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish