Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ በፕሮግራም በጀት አዘገጃጀትና አተገባበር ዙሪያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ 

ሐረር፣ሰኔ 4/2017(ሐክመኮ):-በሐረሪ ክልል በፕሮግራም በጀት አዘገጃጀትና አተገባበር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

በሐረሪ ክልል የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ እና ኘላን ኮሚሽን በፕሮግራም በጀት አስተዳደር ማሻሻያና ቀጣይ አተገባበር ላይ ያተኮረ 

ስልጠና  ለክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ ዓመራሮች ተሰጥቷል።

የሐረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ አቶ መሃመድ ያህያ መርሀ ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለፁት መርሀ-ግብሩ የፕሮግራም በጀትን በአግባቡ ለታለመለት አላማ ለማዋል የሚያስችል አሰራርን ለመተግበር ያለመ ነው።

የመንግስትን በጀት ለታለመለት ዓላማ ማዋል የምናልመው የብልጽግና ማማ ላይ ለመድረስ የሚያግዝ መሆኑንም ገልፀዋል።

በነባሩ የበጀት አሰራር ላይ የነበሩ ከውጤት ጋር ያለመቀናጀት ችግር ለመቅረፍ፣ የሃብት አመዳደብ፣ ግልፅነትና ተጠያቂነትን ያካተተ የበጀት አመዳደብ እንዲኖር ለማስቻል አዲሱ የበጀት አሰራር አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱንም አክለዋል።

የፕሮግራም በጀት አሰራር ፣የፕሮግራም አደረጃጀትን  በመጠቀም ሃብትን ውጤታማ በሆነ መንገድ  ለመመደብ የሚያግዝ እንደሆነም ተመላክቷል።

በተለይ አዲሱ የፕሮግራም በጀት አስተዳደር፣ የእቅድ በጀት ትስስርን በመፍጠር፣ መደበኛና ካፒታል መጪዎችን ለማቀናጀትና ለመስራት የበጀት አሰተዳደር ነጻነትን በመፍጠር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንደሚያበረክትም ገልፀዋል። 

በ2018 በጀት አመት በሁሉም ባለ በጀት መስሪያቤቶች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራና በትግበራ ሂደቱ አስፈላጊው የድጋፍና ክትትል ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ መንግስት ተቋመማት የስራ ኃላፊዎች፣ የወረዳ አመራሮችና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish