በሐረር ከተማ ተሻሽሎ ወደ ስራ የገባውን የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ደንብ በመተላለፍ አካባቢ ያቆሸሹ 8 ሆቴሎች በብር መቀጮ ተቀጡ-የሐረሪ ክልል ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት
ሐረር፣ሰኔ 11/2017(ሐክመኮ):-በሐረር ከተማ ተሻሽሎ ወደ ስራ የገባውን የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ደንብ በመተላለፍ አካባቢ ያቆሸሹ 8 ሆቴሎች በብር መቀጮ መቀጣታቸውን የሐረሪ ክልል ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት አስታወቀ።
የሐረሪ ክልል ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድ አብደላ እንደገለፁት ፅ/ቤቱ በክልሉ ተሻሽሎ ወደ ስራ የገባውን የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ደንብ ተግባራዊ ለማድረግ ጥብቅ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
ፅ/ቤቱ እያከናወነው በሚገኘው የቁጥጥር ስራም ደንቡን ተላልፈው የተገኙ 8 ሆቴሎችና ግለሰቦች በብር መቀጮ እንዲቀጡ መደረጉን አስታውቋል።
ፅ/ቤቱ ተሻሽሎ ወደ ስራ የገባው የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ደንብን በተመለከተ ለማህበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫዎችን ሲሰጥ መቆየቱንም ገልፀዋል።
የከተማዋን ውበትና ፅዳት ለመጠበቅ ተሻሽሎ ወደ ስራ የገባው የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ደንብ ተፈፃሚ ለማድረግ ፅ/ቤቱ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ያሉት ሀላፊው ማህበረሰቡም ለደንቡ ተገዢ በመሆን የአካባቢውን ፅዳትና ውበት ሊጠብቅ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፅ/ቤቱ ደንቡን በሚተላለፉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ መውሰድ የጀመረውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።
0 Comments