Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በሀረሪ ክልል ልማትን በማጠናከር የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል- አቶ ኦርዲን በድሪ

በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን በማጠናከር የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እየተካሄደ በሚገኘው የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 8ኛ መደበኛ ጉባዔ የክልሉ መንግስት በ2018 የበጀት አመት ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮችን በተመለከተ እቅድ አቅርበዋል።

ባቀረቡት እቅድም በ2018 የበጀት አመት ህዝብን በማሳተፍ የክልሉን ሰላም ዘላቂ ለማድረግና የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራዎች በትኩረት ይሰራሉ ብለዋል።

አብሮነትን፣ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን የሚሸረሽሩ አዝማሚያዎችን በመለየትና በመታገል ክልሉ የሚታወቅበትን የሰላም የመቻቻልና የአብሮነት እሴት እንዲሰርፀ ትኩረት ይሰጣል ሲሉ ተናግረዋል።

በቱሪዝም ዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙ ውጤታማ ስራዎች በማጠናከር እያደገ የመጣውን የዘርፉ ተጠቃሚነት የበለጠ እንዲጎለብት የማድረግና የዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚሰራም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

በከተማው የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎችን የማጠናከር እና በገጠር ኮሪደር ልማት በሶስቱም የገጠር ወረዳዎች የአርሶ አደሩን የአኗኗር ዘይቤ ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀየር የሚያስችሉ ስራዎች ይከናወናሉ ብለዋል።

በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍም የተጀመሩ ኢኖቬሽኖችን ስኬታማ የማድረግና ለዲጂታል መሰረተ ልማቶች ቅድሚያ እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

የክልሉን የገቢ አቅምን ለማሳደግና ዘላቂ የገቢ መሰረት ለመገንባት የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚሰሩ ጠቁመው የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማጎልበት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ በትኩረት እንደሚሰራ ነው የተናገሩት።

ከዚህ በተለይም በክልሉ ከተማ ፕላን በመጠበቅ ዘመናዊ መሰረተ ልማት መገንባት ለገጠሩ አካባቢ የተዘጋጀውን መሰረታዊ ፕላን ለመተግበር በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት።

በተለያዩ አማራጮች የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ለማሻሻል እንዲሁም የሚታዩ ውስንነቶችን በመቅረፍ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ተደራሽነትን ለማሳደግና ለአካባቢው ጥበቃ ስራዎች ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

የትምህርት ጥራትን የማሳደግና የማህበረሰቡና ሁለንተናዊ ጤናን የመጠበቅ ስራ ሌሎች በትኩረት የሚከወኑ ተግባራት መሆናቸውን ጠቅሰው በሚከናወኑ ተግባራትም ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚነት ይደረጋል ብለዋል።

በክልሉ ህዝብን እያማረሩ የሚገኙ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍና የህዝብን እርካታ ለመጨመር በትኩረት ይሰራል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የህዝብ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልም ”የሀረር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት” ስራ እንደሚጀምር ገልፀዋል።

እንዲሁም በክልሉ የሚታየውን ብልሹ አሰራርና ሌብነትን በማጥፋት ተጠያቂነት ስርዓት የማስፈን ስራ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል።

ከዚህ ባሻገርም በ2018 የበጀት አመት የሚካሄደውን 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ የክልሉ መንግስት ከምርጫ ቦርድ ጋር በመቀናጀት ዝግጅት የማድረግ የምርጫ ሂደቱን ሰላማዊና ግልፅና ተዓማኒነት ያለው መሆኑን ያረጋግጣል ብለዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish