Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በተገኙበት 18ኛው ብሄራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በሀረሪ ክልል ተከብሯል።

ሀረር፣ጥቅምት 3/2018(ሀክመኮ):-ሠንደቅ ዓላማ ከአባቶቻችን የወረስነው የማንነታችን መለያ የእኛነታችን ጌጥ ነው ሲሉ የሀረሪ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሄኖክ ሙሉነህ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በተገኙበት 18ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሀረሪ ክልል ተከብሯል።

ዕለቱ “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!” በሚል መሪ ቃል ነው የተከበረው።

በመርሀ ግብሩ ላይ የሀረሪ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሄኖክ ሙሉነህ እንደገለፁት ሠንደቅ ዓላማ ከአባቶቻችን የወረስነው የማንነታችን መለያ የእኛነታችን ጌጥ ነው።

ሠንደቅ ዓላማ የብሔራዊ አንድነት መገለጫ፤ የአንድ አገር ዜጎች አገራዊ ፍቅርና ብሔራዊ ስሜትን የሚገልፁበት፤ ታሪካዊ ትስስርና ስነ-ልቦናዊ አንድነትን የሚንፀባረቁበት የአገራዊ አንድነትና ህብረት አርማ ነው ብለዋል።

ሠንደቅ ዓላማ አርማ ብቻ ሳይሆን ከአባቶቻችን የወረስነው የማንነታችን መገለጫ ነው።

ሠንደቅ ዓላማ አባቶቻችን እና እናቶቻችን መስዋእትነት ከፍለው ከዘመን ዘመን አሻግረው የሰጡን የማንነት መለያ ነው።

የሠንደቅ ዓላማ ቀን መከበሩ ሕብረ ብሔራዊ አንድነታችንና ሉዓላዊነታችን በማስጠበቅ የኢትዮጵያን የከፍታ ብሥራትና ሕዳሴ ለማረጋገጥ ለሀገር ክብርና ጥቅም ሁሉም ዜጋ የሚጠበቅበትን ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት በሠንደቅ ዓላማ ፊት ዳግም ቃሉን የሚያድስበት ዕለት ነው ብለዋል።

ዕለቱ ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል እና በሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ መሐላ በመፈፀም እንዲሁም የኢትዮጵያን ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራትና ማንሰራራት በሚያረጋግጡ በልዩ ልዩ ደማቅ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።

ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ሰኞ እንዲከበር በህግ ተደንግጓል።

በመርሀ-ግብሩ ላይ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣የሀረረ ብሄራዊ ጉባኤ አፈ-ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድ፣በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ፣የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድ፣ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር፣በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሀረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙክታር ሳሊህ ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish