Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ርዕሰ መስተዳድሩ በአገልግሎት አሰጣጥና የልማት ስራዎች ላይ ከወረዳ አስተዳዳሪዎች ጋር ተወያይተዋል

ሀረር፣መስከረም 30/2018(ሀክመኮ):-የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በአገልግሎት አሰጣጥና የልማት ስራዎች ላይ ከወረዳ አስተዳዳሪዎች ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም ርዕሰ መስተዳድሩ እንደተናገሩት የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል ረገድ ልዩ ትኩረት መስጠት ወሳኝ ነው።

በወረዳዎች የማህበረሰቡን የአገልግሎት አሰጣት በማሻሻል ፍትሀዊ ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ መንቀሳቀስ እንደሚገባ ነው ያነሱት።

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከልና በማረም የመልካም አስተዳደርን ከማስፈን የልማት ስራ ከማፋጠን ጎን ለጎን ለፀጥታ ጥበቃ ስራዎች ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።

በገቢ ረገድም መሰብሰብ የሚገባውን ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ በክልሉ በኮሪደር ልማት የተመዘገበውን ውጤት ለማስፋት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

ሀረር ከተማ በፕላን እና ስርዓት እንድትመራ ለማድረግ ይሰራል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የኮሪደር ልማት ስራውን በውስጥ ለውስጥ መንገዶች በማስፋት ከዋና መንገዶች ጋር ለማገናኘት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish