Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ፓርቲው የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ ነው

ሐረር፤ መጋቢት 15/2017(ሐክመኮ)፡- ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት በመስጠት እየሰራ መሆኑን የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ምትል ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዱልሀኪም ኡመር ገለፁ።

በብልፅግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ የወጣቶች ክንፍ ፓርቲው ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ ከክልሉ ወጣት ክንፍ አባላት ጋር ተወያይቷል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዱልሀኪም ኡመር እንደገለፁት ፓርቲው የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው።

ፓርቲው ባካሄደው ሁለተኛ ጉባኤው ላይ ከጉባኤ እስከ ጉባኤ በሚከናወኑ ተግባራት ለይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ቃሉን ማደሱንም አቶ አብዱልሀኪም ገልፀዋል።

ወጣቱ በለውጥ ሂደቱ አበርክቶው የጎላ መሆኑን በመጠቆም ፓርቲው ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤው ላሳለፋቸው ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ተፈፃሚነት ተሳትፎውን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አፅንኦት ሰተዋል።

የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ  ወጣት ሙስጠፋ ኢሊያስ በበኩሉ ፓርቲው ከምስረታው ጀምሮ ባስመዘገባቸው ስኬቶች የወጣቱ አበርክቶ የጎላ መሆኑን ገልፀዋል።

ፓርቲው የወጣቱን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን በመጠቆም በሁለተኛው ጉባኤ ፓርቲው ላስቀምጣቸው አቅጣጫዎች እና ውሳኔዎች ተፈፃሚነት ከምን ግዜውም በላይ መስራት ይጠበቅብናል ብሏል።

በመድረኩ ላይ በወጣቶች ክንፍ ስራ አስፈፃሚ አባል ወጣት ስማቸው ደምለው የውይይት መነሻ ፅሁፍ ቀርቦ ከወጣት ክንፍ አባላቱ ጋር ውይይት ተደርጎበታል።

በውይይት መድረኩ ላይ የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ አብዱልሀኪም ኡመር፤የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፤የወጣት ክንፍ ስራ አስፈፃሚዎች እና አመራሮች እንዲሁም የወጣት ክንፍ አባላት ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish