ፓርቲው በመጀመሪያው ጉባኤ ላይ የገባውን ቃል በተግባር በመፈፀም ቃሉን ባህል አድርጎ እየሰራ ይገኛል:- አቶ ጌቱ ወዬሳ
ሀረር ጥር 8/2017(ሀክመኮ):-የብልፅግና ፓርቲ በመጀመሪያው ጉባኤ የገባውን ቃል በተግባር በመፈፀም ቃሉን ባህል አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ የብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለፁ።
በሀረሪ ክልል ከከፍተኛ አመራሮች ጀምሮ እስከ ወረዳ መሰረታዊ ድርጅት ድረስ “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረው የሁለተኛው ጉባኤ ቅድመ ኮንፍረንስ መጠናቀቁን በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለፁ።
አቶ ጌቱ ወዬሳ ኮንፍረንሱ መጠናቀቁን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ፓርቲው በአንደኛው ጉባኤው ለህዝብ የባውን ቃል እውን በማድረግ በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበ እና እያስመዘገበ የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል።
የብልፅግና ፓርቲ የልማት ፕሮጀክቶችን በአጭር ግዜ ጀምሮ በጥራት በማከናወን ቀድሞ የነበረውን የስራ ባህል የቀየረ ፓርቲ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
በተለይ ህብረብሄራዊነት እና አንድነትን በማጎልበት በአመራሩ መካከል በተፈጠረው የወንድማማችነት እና እህትማማችነትን መንፈስ የአገሪቱን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስብራቶች በመጠገን ብሎም ማህበራዊ እሴቶችን በማጎልበት አሻጋሪ ፕሮግራሞችን ቀርፆ በመተግበር በሁሉም ዘርፍ ተጨባጭ ድሎችን ማስመዝገብ የቻለ መሆኑን ገልፀዋል።
በክልሉ በተፈጠረው ጠንካራ የስራ ባህል በልማት ስራዎች፤የመልካም አስተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ እመርታዊ ውጤቶች እየተመዘገቡ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።
ሲካሄድ የነበረው የቅድመ ጉባኤ ኮንፍረንስም የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነትን ይበልጥ በማጎልበት ለቀጣይ ተልዕኮ እና ስኬት ለአመራሩ አቅም የተፈጠረበት መሆኑን አክለዋል።
ኮንፈረንሱ በክልሉ ሁሉም የመንግስት ተቋማት እና በወረዳዎች የሚገኙ የመሰረታዊ ድርጅቶች የተሳተፉበት ሲሆን የዲሞክራሲ ባህል እየዳበረ መምጣቱ የታየበት መሆኑንም አቶ ጌቱ ወዬሳ ገልፀዋል።
በክልል ደረጃ በተካሄደው የማጠቃለያ ኮንፍረንስ በቀጣይ በሚካሄደው የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ የሚሳተፉ አባላትን በዲሞክራሲያዊ መንገድ በመምረጥ መጠናቀቁን ገልጸዋል።
0 Comments