Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ፓርቲው ሁለንተናዊ ብልፅግናን በማረጋገጥ አበረታች ውጤቶችን አስመዝግቧል-አቶ ጌቱ ወዬሳ 

ሐረር፤የካቲት 22/2017(ሐክመኮ):-የብልፅግና ፓርቲ ሁለንተናዊ ብልፅግናን በማረጋገጥ አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሉን በብልፅግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለፁ።

በምርጫ ማግስት ለህዝብ ቃል የተገቡ ልማቶችን፤የብሔራዊ ትርክት ግንባታ፤አገልግሎት አሰጣጥን ማሳደግ እና የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ብልፅግና በማረጋገጥ ረገድ ባለፉት 6 ወራት አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለፁ።

በተለይ ፓርቲው ቅቡልነት ያለው የሀገረ መንግስት ስርዓትን በመገንባት፤ የሕዝብ ተሳትፎ፣ ተጠቃሚነትና እርካታን በማረጋገጥ ረገድ ባከናወናቸው ተግባራት አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ነው አቶ ጌቱ የገለፁት።

ለውጥ አምጭ እሳቤዎችን በመላበስና በመተግበር፣የህዝቡን የአብሮነት እና የመረዳዳት እሴቶች በማዳበር፣ሰላምን በማስፍን እና ህዝቡን በልማት ስራዎች በማሳተፍ አበረታች ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።

አባልና አመራሩ በፓርቲው እሳቤዎችና አቋሞች ላይ የጠራ ግንዛቤና አመለካከት እንዲኖራቸው በማድረግ ረገድ ፓርቲው “የህልም ጉልበት እምርታዊ እድገት”በሚል ስያሜ እና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠናዎች መሰጠታቸውን ገልጸዋል።

በተለይ ማህበረሰቡን በማሳተፍ በተለዩ 11 ዘርፎች የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን ተችሏል ብለዋል።

ከዚህ ውስጥም ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ በተከናወኑ የበጎ ፈቃድ ተግባራት ከ 114 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው አገልግሎትቶችን በመስጠት አቅመ ደከማ ዜጎችን በማህበራዊ እና ኢኮኖሚ ዘርፎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።

በዚህም የበርካታ አረጋውያን እና አቅመ ደካማ ዜጎችን መኖሪያ ቤቶች አድሶ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ መቻሉን አክለዋል።

ከ 4 ሺ በላይ ለሚሆኑ የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ተማሪዎች በኢኮኖሚ ውስንነት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይርቁ ማድረግ መቻሉንም ጠቅሰዋል ።

በተለይ በትምህርት ቤት ምገባዎች ከ 38 ሺ በላይ ተማሪዎች እንዲታቀፉ መደረጉንና በዚህም የተማሪ ወላጆችን የኢኮኖሚ ጫና መቀነስ መቻሉን ገልፀዋል።

ከዚህ ባለፈም በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የአካባቢን ሰላም በማስጠበቅ፣ በፅዳት፣ በአረንጓዴ አሻራ፣በደም ልገሳ፣በማጠናከሪያ ትምህርት እና ሌሎች ዘርፎች ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀዋል።

ከተሞችን የገጠሩ ጥገኛ አድርጎ የማሰብ የቀድሞ ዝንባሌዎችን በማስቀረትም ከተማ እና ገጠሩን በልማት በማስተሳሰር አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን አክለዋል።

በዚህም በኮሪደር ልማት የሀረር ከተማን ፅዱ፤ውብ እና ለኑሮ ምቹ በማድረግ አበረታች ተግባራትን ማከናወን ተችሏል።

ፓርቲው ለቱሪዝም መዳረሻ ልማት በሰጠው ትኩረትም በክልሉ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ማልማት መቻሉን ብሎም ከመደመር መፅሀፍ ሽያጭ በተገኘ ገቢ እና በክልሉ መንግሥት በተመደበ በጀት የተገነባውን ኢኮ ፓርክ ወደ ስራ በማስገባት በዘርፉ መነቃቃት ተፈጥሯል ብለዋል።

በተለይ ጠንካራ የፓርቲ ተቋም በመፍጠር፣ የውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲን እና የአሰራር ግልጽነትን በማስፈን፤የክትትልና ቁጥጥር ስርዓት በማበጀት ተቋማትን ሪፎርም ማድረግ ተችሏል።

በዚህም ብልሹ አሰራሮችን በመታገል የተቋማት አገልግሎት አሳጣጥን ፈጣን እና ቀልጣፋ በማድረግ የተገልጋዩን እርካታ በማሻሻል ረገድ አበረታች ውጤቶች ማስመዝገብ መቻሉን አስረድተዋል።

በክልሉ ባለፉት 6 ወራት በሁሉም ዘርፎች የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶች በአመለካከትና በተግባር የተዋሃደ አመራር መፍጠር በመቻሉ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ጌቱ ወዬሳ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ይበልጥ ለማረጋገጥ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish