ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ከሰጡት ምላሽ እና ማብራሪያ፡-
👉 ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዋለታ ነው። የወጪ ንግድ ገቢያችን ዋልታም ነው።
👉 ኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካን ከ40 ወራት በኋላ አስመርቃ ሥራ ላይ ታውላለች
👉 ግብርና በዚህ ዓመት 6 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት እንዲያመጣ ነው የታቀደው
👉 23 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ከሴፍቲኔት ተረጂነት ነጻ ወጥተዋል። ይህ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ማሳያ ስለሆነ ኩራት ሊሰማን ይገባል
👉ቀሪ ከ4 ሚሊዮን በላይ የሴፍቲኔት ተረጂዎችን ነጻ ለማውጣት ኢትዮጵየን ሙሉ ለሙሉ የምግብ ሉዓላዊነቷን ያረጋገጠች ሀገር ማድረግ አለብን
👉በአዲስ አበባ ደረጃ በተከናወኑ ስራዎች የሀገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል
👉 በዘንድሮው ዓመት በኢትዮጵያ ከ150 በላይ ዓለም አቀፍ ኮንፍረንሶችን ማስተናገድ ተችሏል ።ይህም አምና ከነበረው ከፍተኛ ብልጫ አለው
👉በኢንዱስትሪ ዘርፍ ዘንድሮ 12 በመቶ ገደማ ዕድገት ለማምጣት ታቅዶ እየተሰራ ነው
👉ኢትዮጵያ ሰፊ ፈተና ቢኖርባትም በመላው ሕዝብ ትብብር ባለፈው ዓመት የ8 ነጥብ 1 በመቶ እድገት ማምጣት ተችሏል
👉የኢትዮጵያ ታምርት የማምረት አቅም አምና 59 በመቶ ነበር የደረሰው፤ ዘንድሮ 65 በመቶ ደርሷል
👉የመስታወት ፋብርካ በዓመት 600 ሺህ ቶን ገደማ የሚያመርት እየገነባ ይገኛል።
👉ወደ ማክሮ ኢኮኖሚ ያስገቡን ጉዳዮች አንዱ የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶች ናቸው፤ በስራ አጥነት፣ በዋጋ ግሽበት፣ በወጪና ገቢ ንግድ ሚዛን መጓደል ሊገለፅ የሚችል ነው። ሁለተኛው ለግሉ ዘርፍ የስራ አካባቢው ምቹ አልነበረም። ሶስተኛው ምርታማነት ነው።አራተኛው ተወዳዳሪ የኢኮኖሚ ሁኔታ አለመፈጠሩ።
0 Comments