Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ በትኩረት መስራት ይገባል- አቶ ጌቱ ወዬሳ

ሀረር ታህሳስ 11/2017(ሀክመኮ):-ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ የማህበረሰቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ በትኩረት መስራት እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለፁ።

በሀረሪ ክልል የክልሉን ገቢ ለማሳደግ በተዘጋጀው የ 3 ወራት መርሀ ግብር ላይ ውይይት ተካሂዶበታል።

የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ በወይይቱ ላይ እንደገፁት የማህበረሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ገቢን የመሰብሰብ አቅምን ማጎልበት ይገባል።

በመሆኑም ባለፉት ወራት ሳይሰበሰቡ የቀሩ ተሰብሳቢ ብሮችን በተገቢው መንገድ በመሰብሰብ የክልሉን የልማት እንቅስቃሴ ማፋጠን እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በተለይ ወረዳዎች በክልሉ የአከራይ ተከራይ ስርዓትን ወደ ህጋዊ መንገድ በማምጣት ከዘርፉ መሰብሰብ የሚገባውን ግብር በአግባቡ ለመሰብሰብ ትኩረት ሰተው እንዲሰሩ አሳስበዋል።

በሌላ በኩል ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ እና የአየር ላይ ንግድን ስርዓት በማስያዝ ወደ ህጋዊ የንግድ ስርዓት ለማምጣት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር በበኩላቸው እያንዳንዱ የመንግስት ተቋማት ዕና ወረዳዎች ተሰብስበው ለመንግስት ገቢ ያልሆኑ ብሮችን ገቢ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል።

በገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ ያሉትን የቅንጅታዊ አሰራር ችግሮች በመቅረፍ የህግ የበላይነትን ማስከበር እንደሚገባም ጠቁመዋል።

በተለይ በኢንቨስትመንት መሬት ወስደው ሊዝ ሳይከፍሉ አጥረው የተቀመጡትን ክፍያ እንዲፈፅሙ እና ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረግ እንደሚገባ  ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish