Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የአገልግሎት አሰጣጥን ውጤታማ ማድረግ ተችሏል

ሐረር፤መጋቢት 18/2017(ሐክመኮ):-በሀረሪ ክልል በሚገኙ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ውጤታማና ተደራሽነትን ማድረግ መቻሉን የሀረሪ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ።

የተቋሙ ኃላፊ አቶ ጀማል ኢብራሂም ባለፉት ሰባት የለውጥ አመታት መንግስት ትኩረት ከሰጣቸው ጉዳዮች መካከል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፉን ማሳደግ አንዱ መሆኑን በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል።

በዚህም ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ውጤታማና  ተደራሽ የማድረግ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተከናወኑ እንደሚገኙ ነው ሀላፊው የጠቆሙት።

በተለይ ከለውጡ በፊት የነበሩ አሳሪ ህጎችን በማሻሻልና ለዘርፉ እድገት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ፖሊሲዎችን በማውጣት ዘርፉን የማዘመንና ከጊዜው ጋር መራመድ የሚያስችል አሰራር መገንባት የተቻለበት መሆኑንም አክለዋል።

በዚህም የመንግስት ተቋማት የደንበኞችና የተቋማት የመረጃ (ሰነድ)አያያዝን በዲጂታል በመቀየር ደህንነቱ የተጠበቀ ግልጽና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ እገዛ ማድረጉንም ገልጸዋል።

የመንግስት አገልግሎት መስጫዎችን ወደ አንድ ቋት በማስገባት ሀሰተኛ ሰነድ እና የመረጃ ማጭበርበር ችግሮችን ለመከላከል ያስቻለ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በቀጣይም መንግስተ ሊገነባው ላቀደው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታና የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማዘመን በትኩረት የሚሰራ መሆኑን አቶ ጀማል ኢብራሂም ገልፀዋል

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish