Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የገጠር ኮሪደር ልማት የአርሶ አደሩን ሕይወት ለመቀየር ከፍተኛ አበርክቶ ይኖረዋል-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ 

ሐረር፣ሰኔ 16/2017(ሐክመኮ):-የገጠር ኮሪደር ልማት የአርሶ አደሩን ሕይወት ለመቀየር ከፍተኛ አበርክቶ እንደሚኖረው የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ። 

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ በቀጣይ 2018

ተግባራዊ የሚደረገውን የገጠር ኮሪደር ልማት ስራ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንደገፁት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ ከተሞችን የተሻለ ገፅታ ማላበስ አስችሏል። 

በተለይ ከተሞች በስርዓት የሚመሩ ውብና ፅዱ እንዲሆኑ በማስቻል ለዜጎች ምቹ የመኖሪያ አካባቢን የፈጠረ መሆኑን ጠቁመዋል። 

በሐረር ከተማም በኮሪደር ልማት ዘርፍ አበረታች ውጤቶች የተገኙ ሲሆን በቀጣይ 2018 ለገጠር ኮሪደር ልማት ስራ ትኩረቱ በመስጠት በከተማ የተመዘገበውን ውጤት በገጠሩ ክፍል ለማስፋት እንደሚሰራ ገልፀዋል። 

በተለይ በገጠር አካባቢ የሚከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች የአርሶ አደሩን የአኗኗር ዘዬ ለመቀየር የሚያስችሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል። 

ለአብነትም አርሶ አደሩ ያለውን ሀብትና ፀጋ በአግባቡ ተጠቅሞ ኢኮኖሚውን በማሳደግ በዚያው ልክ ሕይወቱን እንዲመራ በማስቻል በቤተሰብ ደረጃ የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል የሚያግዝ ነው። 

በተለይ በገጠር እና በከተማ መካከል ያለውን የአኗኗር ዘዬ ልዩነት በማጥበብ ማህበረሰቡ በቀላሉ የሚገናኝበትን ዕድል በመፍጠር ጠንካራ ማህበራዊ ትስስር እንዲፈጠር የሚያስችል መሆኑንም አክለዋል፡፡ 

በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ለገጠር ኮሪደር ልማት ስራዎች ስኬታማነት ትኩረት በመስጠት የተያዘው እቅድ ተፈጻሚ እንዲሆን ርብርብ ሊያደርጉ እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል። 

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish