የዜጎችን የጎዳና ተዳዳሪነት እና የጎዳና ላይ ልመና ተጋላጭነትን ለመከላከል እየተሰራ ነው – አቶ አዩብ አህመድ
በሀረሪ ክልል ኑሮአቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ዜጎችን ከጎዳና ህይወት ለማላቀቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ አዩብ አህመድ ገለጹ።
በክልሉ የጎዳና ተዳዳሪ ዜጎችን ህይወት ለመቀየር ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን ኮሚቴው ባለፉት ሶስት ወራት ያከናወናቸውን ተግባራት ገምግሟል።
በወቅቱም የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አቶ አዩብ አህመድ እንደገለፁት የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ለማስከበር እና ከጎዳና ተዳዳሪነት ህይወት ለማላቀቅ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ትኩረት ተሰቷል ።
በተለይ ማህበራዊ ቀውሶችን ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን የጎዳና ተዳዳሪነት ህይወት ለማስቀረት ልዩ ትኩረት ተሰቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በቀጣይም ለጎዳና ተዳዳሪነትና ጎዳና ለይ ልመና መንስኤ እየሆኑ የሚገኙ ማህበራዊ ቀውሶችን በተቀናጀ ሁኔታ ለመቅረፍ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
ኮሚቴው በክልሉ የዜጎችን ጎዳና ተዳደሪነት እና ለጎዳና ለይ ልመና ተጋላጭነትን ለመቀነስ እና ለመከለከል የሚያስችል የህግ ማዕቀፍን ለመተግበር ወደ ስራ መግባቱን አቶ አዩብ አህመድ ጠቁመዋል።



0 Comments