Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የዘንድሮው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል አብሮነትና ወንድማማችነትን ይበልጥ አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ ይከበራል-ምክትል አፈ-ጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድ

ሀረር፣ጥቅምት 18/2018(ሀክመኮ):-የዘንድሮው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል አብሮነትና ወንድማማችነትን ይበልጥ አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ እንደሚከበር የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድ ገለፁ።

20 ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል አከባበር አብይ ኮሚቴ በዓሉን ለማክበር በቀረበው መነሻ ዕቅድ ላይ ተወያየ።

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድ በውይይቱ ላይ እንደገለፁት
የብሄር ብሄረሰቦች ቀን መከበሩ በተለይም እንደ ሀገር አንድነትን በማጎልበት የጋራ ትርክትን በመገንባት የወንድማማችነት እሴት እንዲጎለብት ማስቻሉን ገልፀዋል።

ዘንድሮ ለ 20ኛ ግዜ የሚከበረው በዓሉን አብሮነትና ወንድማማችነትን ይበልጥ አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

በዓሉ የህዳሴ ግድብ ምረቃ በተከናወነበትና ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር እንቅስቃሴ እየተደረገ ባለበት ወቅት መከበሩ ዕለቱን ለየት እንደሚያደርገው በመጠቆም በዓሉ ሀገራዊ መግባባትና አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ እንደሚከበር ገልጸዋል።

በዓሉን የክልሉን ልማትና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በሚያጎለብቱ መርሐግብሮች ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው።

በዓሉ በፌዴራሊዝምና ህገ መንግስት አስተምህሮት የፓናል ውይይቶች፣በስፖርታዊ ውይይቶች፣በፅዳት ዘመቻ፣በደም ልገሳ፣በጥያቄና መልስ ውድድሮች፣በሙዚየም ጉብኝት፣የገጠር ኮሪደር ልማቶችን በጉልበት በማገዝ፣በተቋማትና ትምህርት ቤቶች በባሀላዊ ምግቦችና ውዝዋዜዎች ይከበራል ብለዋል።

በውይይቱ ላይ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ አሪፍ መሃመድ፣ የክልሉ ሴክተር መስሪያ ቤት ሃላፊዎችና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

ዘንድሮ የሚከበረው 20 ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በሆሳህና ከተማ”ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ይከበራል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish