የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜና ጥራት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው – አቶ ኦርዲን በድሪ
የኮሪደር ልማቱን በምሽት ጭምር በማከናወን ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜና ጥራት ለማጠናቀቅ እየተሰራ እንደሚገኝ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።
ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ በምሽት እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በምልከታው ወቅት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለፁት የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና ጥራት ለማጠናቀቅ ስራውን በምሽት ጭምር በማከናወን መነቃቃት ተፈጥሯል።
የኮሪደር ልማቱ ፕሮጀክቶችን በምሽት ጭምር የማከናወን ልምድ እንዲዳብር በማድረግ ቀድሞ የነበረውን የስራ ባህል የቀየረ መሆኑንም ገልፀዋል።
ስራው በተለይ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ በጥራት እና ፍጥነት በማጠናቀቅ ለቀጣይ የልማት ስራዎች ልምድ የተወሰደበት ነው ብለዋል።
ማህበረሰቡ ለኮሪደር ልማቱ እያደረገው ያለው ድጋፍ ለስራው ምቹ ሁኔታን መፍጠሩን በመጠቆም አጋጣሚውን በመጠቀም ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜና ጥራት ለማከናወን እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
የኮሪደር ልማት ስራውን በአጭር ግዜ በማጠናቀቅ ምቹ የመኖሪያ እና መስሪያ ከተማን ለመፍጠር ርብርብ እንደሚደረግም ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተናግረዋል።



0 Comments