የኮሪደር ልማቱ ከተሞቻችን ለረጅም ዓመታት የቆዩበትን ቆሻሻና አረንቋ በማስወገድና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ጽዱ አካባቢን እየፈጠረ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
የኮሪደር ልማቱ ከተሞቻችንና አካባቢያችን ለረጅም ዓመታት የቆዩበትን ቆሻሻና አረንቋ በማስወገድና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ጽዱ አካባቢን እየፈጠረ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኮሪደር ልማትን በተመለከተ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም የኮሪደር ልማቱ ከተሞቻችንና አካባቢያችን ለረጅም ዓመታት የቆዩበትን ቆሻሻና አረንቋ በማስወገድና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ጽዱ አካባቢን እየፈጠረ ነው ብለዋል።
አዲስ አበባ ላይ የመጣው የኮሪደር ልማት ለውጥ በራስ የፋይናንስ አቅም፣ በራስ እውቀት እና በዚህ አስገራሚ ደረጃ መገንባቱ ብዙዎችን እያስደነቀ መሆኑን ገልጸዋል።
የነዋሪዎችን አኗኗር አሻሽሏል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮሪደር ልማቱ አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አካበቢዎች ነው ለዚህም ጎንደር፣ ጅማ፣ ባህርዳር፣ ቢሾፍቱና ሌሎችም ብዙ ከተሞች እየተዋቡ እየተቀየሩ ነው ብለዋል።
ከተሞችን ጨምሮ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች እስከ ነሐሴ መጨረሻ ድረስ ከ20ሺህ በላይ ፕሮጀክቶች እንደሚመረቁም አስታውቀዋል።
እነዚህም መንገድ፣ ጤና ጣቢያ፣ ትምህርት ቤትና ሌሎች በርካታ መሰረተ ልማቶችን ያካተቱ መሆናቸውን ጠቁመው ይህ ስንተባበር ከተማንም ሀገርንም የመቀየር አቅም እንዳለን ማሳያ ነው ብለዋል።
0 Comments