የክልሉ ህዝብ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ እያደረገ የሚገኘውን ንቁ ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ
ሐረር፤ሰኔ 6/2017(ሐክመኮ):-የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤትና በክልሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሄኖክ ሙሉነህ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ገቢ አሰባሰብ ጋር ተያይዞ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ የክልሉ ህዝብ ያልተቋረጠ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
የሕዳሴ ግድብ ለሀገር ሁለንተናዊ ልማት እና ዕድገት የሚኖረው ድርሻ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅትም በክልሉ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በሁሉም የመንግስት እና የግል ኮሌጆችና ትምህርት ቤቶች በቦንድ ሽያጭ ሀብት የማሰባሰብ ስራ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ በሰጡት መግለጫ አመላክተዋል።
ከገቢ አሰባሰብ ስራ በተጨማሪ በህብረተሰቡ ዘንድ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም አክለዋል፡፡
በቀጣይም በክረምት ወራት በከተማ እና በገጠር ወረዳዎች ለግድብ ግንባታ ሀብት ለማሰባሰብ የሚያስችል የውይይት እና የህዝብ ንቅናቄ የመፍጠር ስራዎች እንደሚከናወኑ ጠቁመው በተለይም የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራዎች እንደሚሰራ የገለጹት ኃላፊው በዚህም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራው ውጤታማነት እንደሚያስችል ገልጸዋል።
በክልሉ የተጀመረውን ንቅናቄ ከማጠናከር ባሻገር፣ በቦንድ ሽያጭ እና በ 8100 አጭር የጽሑፍ መልዕክት ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል።
የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ከዳር ለማድረስ ሁሉም ማህበረሰብ በጋራና በአንድነት በመሆን ቀድሞ ሲያደርገው የነበረውን ድጋፍ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
የግድቡ ግንባታ ለፍፃሜ እስከሚደርስ ድረስ ክልሉ ህዝብ እያሳየ ያለው ድጋፍም ማጠናከርና ከተባበርን ካሰብንበት ለመድረስ ሊያስቆመን የሚችል ኃይል እንደማይኖር ማሳየት ይገባል ብለዋል።
የክልሉ ህዝብ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ስኬታማነት እያከናወኑ የሚገኘውን የድጋፍ ስራዎችን አጠናክረው እንዲቀጥሉም አቶ ሄኖክ ጥሪ አቅርአቅርበዋል።
#GrandEthiopianRenaissance #Ethiopia #Sea #water
0 Comments