የከተራና የጥምቀት በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ለማስቻል አስፈላጊውን ዝግጅት ተደርጓል-የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን
በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የከተራና የጥምቀት በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ለማስቻል አስፈላጊውን ዝግጅት መደረጉን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።
ከበአሉ ጋር ተያይዞ መግለጫ የሰጡት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን እንዳሉት በዓላቱ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከበር ለማስቻል ለሁሉም ፈፃሚ አመራር እና አባላት እንዲሁም አጋዥ ተቋማት የበአሉን አከባበር የተመለከተ የፀጥታ እቅድ ወጥቶ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ከማድረግ ጀምሮ ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል።
በአሁን ወቅትም የበአሉ አከባበር ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊ የሰው ኃይል ተመድቦ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።
ኮሚሽነሩ አክለውም ነዋሪው አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ወድያውኑ ለፖሊስ ጥቆማ መስጠት ይገባል ብለዋል።
ኮሚሽነሩ ባስተላለፉት መልዕክትም ሰላም ወዳዱ የክልሉ ህዝብ እንደ ወትሮው ሁሉ አሁንም ከፖሊስና ከሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ጎን እንዲሰራ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
0 Comments