Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የእኛን አርዓያነት ተከትሎ ሁሉም ግብር ከፋይ በታማኝነት ግብሩን መክፈል ይኖርበታል:- ግብር ከፋዮች

በሀረሪ ክልል ታማኝ ግብር ከፍዮች የምስጋናና የዕውቅና ሽልማት መርሐ ግብር ተካሂዷል።

በእውቅና መርሃግብሩ ላይ ያነጋገርናቸው  ግብር ከፋዮችን እንዳሉት ለዚህ ሽልማት የበቃነው በታማኝነትና በሕግ ተገዥነት ግብር በመክፈላችን ነው።

ሀገር የምትገነባው በዕርዳታ ሳይሆን ከምታገኘው የውስጥ ገቢ ነው ያሉት ግብር ከፋዮቹ በተለይም የመንገድ፣ የትምህርት፣ የጤና ፣ የውሃና ሌሎች መሠረተ ልማቶች የተገነቡት የሚገነቡት ውስጥ ገቢ ነው” ብለዋል።

ግብር ከልማት ባሻገርም በኅብረተሰቡ መካከል ፍትሐዊነት የማረጋገጫ መንገድም መሆኑን የሚገልጹት ተሸላሚዎቹ ስለሆነም ግብር መክፈል ያለውን ሁለንተናዊ ጥቅም በመገንዘብ ሁሉም በታማኝነት ግብሩን መክፈል ይኖርበታል ሲሉ ተናግረዋል።

ሀገርን ለማልማትና ከድህነት ለመውጣት ተግቶ መሥራትና ከሚገኘው ገቢ በታማኝነት ግብር መክፈል ለከፋዩም፤ ለሀገርም ክብር መሆኑን ነው የገለጹት።

“ግብር መክፈል ግዴታ ነው። ይህን ግዴታችንን በታማኝነት ግብር በመክፈል ለክልላችን ብሎም ለሀገራችን ዕድገት የበኩላችንን ሚና እየተወጣን እንገኛለን” ብለዋል።

በቀጣይም ይህንን ክብር ለማስጠበቅ ሚናቸውን በማጠናከር በክልሉና በሀገር ልማት ላይ የምናበረክተውን አስተዋፅዖ ለማላቅ ተግተን እንሠራለን ብለዋል።

ሁሉም ነጋዴ በወቅቱና በታማኝነት ግብር በመክፈል ለክልሉና ለሀገሩ ልማት የበኩሉን ድርሻ ማበርከት እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል።

ሁሉም ነጋዴ የእኛን አርዓያነት ተከትሎ በታማኝነት ግብሩን መክፈል ይኖርበታል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በክልሉ በ2016 በጀት ዓመት ታማኝ ግብር ከፋዮች የምስጋናና ዕውቅና መርሐ ግብር የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ  በተገኙበት ነው የተካሄደው።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish