Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የኢትዮጵያ የመንገድ ሽፋን 175 ሺህ ኪሎ ሜትር ደርሷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

የኢትዮጵያ የመንገድ ሽፋን 175 ሺህ ኪሎ ሜትር ደርሷል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የመንገድ መሰረተ ልማትን በተመለከተ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም የኢትዮጵያ የመንገድ ሽፋን 175 ሺህ ኪሎ ሜትር ደርሷል ብለዋል።

1 ነጥብ 5 ትርሊዮን ብር የሚጠይቁ 300 ፕሮጀክቶች መጽደቃቸውን ተናግረው ውል በመፈራረም በተለያየ የስራ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ነው ያሉት።

ከእነዚህ ውስጥ 169 ፕሮጀክቶች ከ11 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ በአሁኑ ወቅት እየተገነባ መሆኑንም ገልጸዋል።

በዚህ ዓመት ከ1 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ ይመረቃል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ 17 ሺህ ኪሎ ሜትር መንገድ የከባድና መካከለኛ ጥገና እየተደረገ ነው ብለዋል።

በአጠቃላይ መንገድ 28 ሺህ ኪሎ ሜትር በጥገና እና በአዲስ እየተገነባ መሆኑን ገልጸው የመንገድ መሰረተ ልማት ሽፋንን የማሳደግ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም አስታውቀዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish