Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ብዝሃ ዘርፍ እንዲሸጋገር የተነደፈው ፖሊሲ በእጅጉ ውጤታማ ሆኗል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ብዝሃ ዘርፍ እንዲሸጋገር የተነደፈው ፖሊሲ በእጅጉ ውጤታማ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች እየሰጡት ባለው ምላሽ እንዳመለከቱት መንግስት ከህዝብ ጋር ተሳስሮ ልማት እንዲያመጣ ግልጽ አቅጣጫ የተቀመጠውም ከለውጡ ወዲህ ነው።

ለአብነትም መንግስትና ህዝብ ተሳስረው በአረንጓዴ አሻራ አማካኝነት 48 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል ችለዋል ብለዋል።

ለዚህ ስኬት ደግሞ ከ25 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ሳይታክቱ በነጻ በየዓመቱ ወጥተው ችግኞችን መትከላቸውን ገልጸው፤ ይህም የመንግስትና ህዝብ ቅንጅትን በተግባር ያሳየ መሆኑን ገልጸዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish