Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የኢትዮጵያ ታምርት የማምረት አቅም አምና ከነበረበት 59 በመቶ ዘንድሮ 65 በመቶ ደርሷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

የኢትዮጵያ ታምርት የማምረት አቅም አምና ከነበረበት 59 በመቶ ዘንድሮ 65 በመቶ መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ኢንዱስትሪን በተመለከተ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም በኢንዱስትሪ ዘርፍ ዘንድሮ 12 በመቶ ገደማ ዕደገት ለማምጣት ታቅዶ ሲሰራ መቆየቱን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ታመርት በሚል ንቅናቄ በጣም ሰፊ ስራዎች ተከናውነዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህም የማምረት አቅም አምና 59 በመቶ እንደነበር አስታውሰው ዘንድሮ 65 በመቶ ደርሷል ብለዋል።

ይህም የፋብሪካዎችን የማምረት አጠቃቀም በማሳደግ ነው ያሉ ሲሆን በዚህ ዓመት የኢንዱስትሪው የኃይል ፍላጎት በ40 በመቶ ደርሷል ነው ያሉት።

ይህ ትልቅ ዕድገት ነው፤ የሲሚንቶ ምርት ከፍ ብሏል፤ በብረት ውጤቶች 18 በመቶ ዕድገት ተመዝግቧል ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ብረት የማምረት አቅም መገንባቷን ጠቁመው የብረት ፍላጎትን ሙሉ ለሙሉ ማሟላት የሚያስችሉ ስራዎች ተጀምረዋል ነው ያሉት።

የመስታወት ፋብርካ በዓመት 600ሺህ ቶን ገደማ የሚያመርት እየተገነባ መሆኑን ገልጸው የፋብሪካው ስራ በማንኛውም መስፈርት አስደናቂ ነው ብለዋል።

በሚቀጥለው ታህሳስ ወይም ጥር ላይ እንደሚጠናቀቅ ጠቅሰው የሶላር ምርት ፓናል ምርት የሚያመርት ፋብርካዎችም እየተገነቡ መሆኑና በቅርቡ ይመረቃሉ፤ ኢንዱስትሪውን ለማነቃቃት እየሰራን ነው ሲሉም ገልጸዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish