Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከነሐሴ 4 ጀምሮ በሀረሪ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ ይጀምራል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በክልሉ የሚካሄደውን የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሀሙድ ድሪር በክልሉ በተለያዩ ወረዳዎች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚሳተፉ አካላት ልየታ ተካሂዷል ብለዋል፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ተገኘወርቅ ጌቱ (ዶ/ር) በበኩላቸው በሂደቱ ተወካዮች የኢትዮጵያን መሰረታዊ ችግሮች ይቀርፋሉ በተባሉ አጀንዳዎች ላይ መክረው ለኮሚሽኑ ያስረክበሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።

ኮሚሽኑ በተለያዩ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተሰባሰቡ አጀንዳዎችን በመጠቀም ወደ አጀንዳ ቀረፃ የሚገባ ሲሆን በክልሉ በሚከናወነው አጀንዳ የማሰባሰብ መድረክ ላይም ከ1ሺህ በላይ ተወካዮች ይሳተፋሉ ተብሏል።

ምክክሩ በህዝቦች መካከል እንዲሁም በህዝብና መንግስት መተማመን ለማምጣት ጉልህ ሚና ያበረክታል ተብሏል።

በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ የማህበረሰብ ወኪሎች፣ በክልሉ የሚገኙ የፖለቲካ የተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ የሶስቱ የመንግስት አካላት ተወካዮች፣ የተለያዩ ተቋማትና ማህበራት ተወካዮች እና የታዋቂና ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተወካዮች ይሳተፋሉ፡፡

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish