Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የአካባቢ ንፅህናን በመጠበቅ ጽዱ፣ውብና ምቹ አካባቢን መፍጠር  ይገባል-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

ሐረር ሰኔ 28/2017(ሐክመኮ):-የአካባቢ ንፅህናን በመጠበቅ ጽዱ፣ውብና ምቹ አካባቢ መፍጠርን ባህል አድርጎ መቀጠል እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

በሐረር ከተማ በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ ችግኞች እንክብካቤና የፅዳት ዘመቻ በዛሬው ዕለት ተካሄደ።

ዘመቻውን ያስጀመሩት የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ መርሀ-ግብሩ የአካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤን ዓላማ ማድረጉን ገልፀዋል።

በጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ (ዶ/ር)ኢንሼቲቪ በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር በክልሉ በርካታ ችግኞች መተከላቸውን በማስታወስ ካሁን ቀደም የተተከሉ ችግኞችን ለመንከባከብ ዘመቻው መካሄዱንም አክለዋል።

የሀገራችን ብሎም የክልላችን የማንሰራራት ታሪክ ተጀምሯል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ዘመቻው በተለይ ማህበረሰቡን ፅዱ፣ውብና ጤናማ በሆነ አካባቢ እንዲኖር የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል።

የአካባቢ ንፅህናን በመጠበቅ ጽዱ፣ውብና ምቹ አካባቢ መፍጠርን ባህል አድርጎ መቀጠል እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በክልሉ በቅርቡ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር እንደሚጀመርም ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል።

በመርሀ-ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር፣የሐረሪ ጉባኤ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አሚና አብዱልከሪምን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish