Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የአረንጓዴ ልማት ስራ የአካባቢ ጸጋዎችን ወደ ሃብት ቀይሯል -የሀረሪ ክልል የዲያስፖራ አባላት

የአረንጓዴ ልማት ስራ የአካባቢ ጸጋዎችን ወደ ሃብት መቀየሩን መመልከታቸውን ከተለያዩ ሀገራት የመጡ የሀረሪ ክልል የዲያስፖራ አባላት ገለጹ።

በሀረሪ ክልል በዛሬው እለት በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ማስጀመሪያና የአንድ ጀምበር 500 ሺህ ችግኞች የመትከል መርሃግብር ላይ የተገኙት የዲያስፖራ አባላት እንዳሉት በአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት የበለጸገች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስተላለፍ የተጀመሩ ጥረቶችን እያሳኩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመረውና መላው ህብረተሰብ እየተሳተፈበት ያለው የአረንጓዴ ልማት ስራ ውጤት ማስገኘቱን ጠቁመዋል።

የአረንጓዴ ልማት ስራ በተለይ የጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች በጎርፍ አደጋ የሚደርሰውን ጉዳት እንዲቀንስ ማስቻሉንም ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈም የአረንጓዴ ልማት ስራዎች የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባለፈም ለወጣቶች የስራ እድል ፈጥሯል ብለዋል።

በእለቱ በተካሄደው የዲያስፖራ አባላቱ እንደየመጡበት አካባቢ የመትከያ ስፍራ መዘጋጀቱ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።

የአረንጓዴ ልማት ተስማሚ ስነ ምህዳር ለትውልድ ለማቆየት፣ የተፈጥሮ ሀብትን በመጠበቅ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም፣ በግብርናው ዘርፍ ደግሞ የሰብልና እንስሳት ሀብት ልማትን ለማሳደግ፣ ጎርፍና መሰል የድርቅ ተፅዕኖዎችን ለመከላከል ያስችላል ብለዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish