Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ በሀረር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጎበኙ

የኢፌዴሪ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዶክተር አለሙ ስሜና የተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች በሀረር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተጎብኝተዋል።

ሚኒስትሩ ዶክተር አለሙ ስሜ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት የኮሪደር ልማቱ በሐረር ከተማ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን ተመልክተናል።

በኮሪደር ልማቱ የተከናወኑና እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችም ታሪካዊቷን የሀረር ከተማ ውብና ፅዱ በማድረግ አዲስ ገፅታ እንድትላበስ እያደረገ ነው ብለዋል።

የኮሪደር ልማቱ በተለይም የትራንስፖርት እንቅስቃሴውን የተሳለጠ እንዲሆን ከማስቻል ባለፈ ለዜጎቹ ምቹ እንዲሆን እያስቻለ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በክልሉ ፍጥነትንና ጥራትን መሰረት ባደረገ መልኩ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች የበለጠ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

ሚኒስትሩና የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች በከተማውና በጁገል አለም አቀፍ ቅርስ ውስጥ የተሰሩና እየተሰሩ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ነው ተዘዋውረው የተመለከቱት።

በጉብኝቱ ላይ የሀረሪ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፣ የኢፌዴሪ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዶክተር አለሙ ስሜና የተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish